በሶማሊ ክልል የተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ” ገዢው ፓርቲ ለህዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል” ተባለ

መስከረም ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የህዝብ ግንኙነት ስራ አማካሪ እና የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበር በመሆን ካገለገለ በሁዋላ የተለያዩ

የቪዲዮ ማስረጃዎችን በመያዝ ከአገር የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን ፣ “ኦ ኦጋዴን” በሚል ኢሳት ያስተላለፈው አጭር የዶክመንታሪ ፊልም፣ በስልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች ለሶማሊ፣

ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ያላቸውን ንቀት ያሳያል ብሎአል።

ዘገባውን ከተመለከተ በሁዋላ ህመም እንደተሰማው የገለጸው አብዱላሂ፣ አስከሬን እንዲለቅሙ ሲገደዱ የነበሩት ሲቪሎች ሁኔታ በእጅጉ እንደረበሸው ገልጿል አንዳንድ የመንግስት ደጋፊዎች

ኦብነግ አካባቢውን ለመገንጠል የሚንቀሳቀስ በመሆኑ፣ በአባለቱና በደጋፊዎቹ ላይ የተወሰደው እርምጃ ትክክል ነው በማለት በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ሲጽፉ ተመልክተናል፣ ለዚህ ምን አስተያየት

አለህ የተባለው አብዱላሂ፣ ” ይህን የሚሉ ሰዎች ማፈር አለባቸው በማለት መልሷል ወጣት አብደዱላሂ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን አስወግደው በአንድነት በመነሳት

በስልጣን ላይ ያለውን ሃይል ማስወገድ እንደሚገባቸውም አብዱላሂ መልእክት አስተላልፏል።

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር /ኦብነግ የአማርኛ ክፍል ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ሃሰን አብዱላሂ በበኩላቸው፣ በክልሉ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት የቆየ መሆኑን ገልጸው፣ ድርጅታቸው

በደቡብ አፍሪካ፣ በሄግ፣ በስዊድንና በጄኔቫ ጉዳዩ ተጣርቶ ተጠያቂ የሚሆኑት ባለስልጣኖች በህግ እንዲጠየቁ አቤቱታ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

መንግስት የተገደሉት የኦብነግ አባላት እንጅ ሲቪሎች አይደሉም በሚል ለማስተባበል ቢሞክር የእናንተ ምላሽ ምን ይሆናል ተብለው የተጠየቁት አቶ ሃሰን፣ መንግስት በራሱ የሚተማመን ከሆነ

አካባቢውን የጦር ቀጠና ማድረጉን ትቶ ለውጭ ጋዜጠኞችና የሰአብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ክፍት በማድረግ አለበት በማለት፣ በክልሉ የሚፈጸመው ጥቃት በህዝቡ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግረዋል።