በሶማሊያ መንግስትና በኬንያ ጦር መካከል ልዩነት መፈጠሩ ተሰማ

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :- በሰላም አስከባሪነት ስም ሶማሊያ የሚገኘው የኬንያ ጦር የሶማሊ ጎሳዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ  አድርጓል የሚል ክስ በሶማሊያ መንግስት ቀርቦበታል።

ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የተጻፈ ደብዳቤ በስህተት ለጋዜጠኞች በመላኩ ዜናው ይፋ መውጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የኬንያ ጦር በኪስማዮ አካባቢ የተለያዩ ጎሳዎች እርስ በርሳቸው እንዲጋጩ በማድረጉ 65 ሰዎች መሞታቸውን ደብዳቤው ይጠቅሳል።

የሶማሊያ መንግስት  በኪስማዩ የሚገኘው የጦር አዛዥ እንዲቀየሩ መጠየቁም ተመልክቷል።