ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ለመጓዝ የሚፈልጉ ስደተኞችን በጫኑ ሁለት ተሽከርካዎች እየተጓዙ በነበረበት ሰአት ላይ ተሽከርካሪዎቹ በመገልበጣቸው በርካቶች አልቀዋል።
የሟቾችን ቁጥር በአሀዝ ለማወቅ አልተቻለም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሶማሊላንድና በፑንትላንድ ድንበር አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያኖች በአደጋው መገልበጣቸውን ቢያስታውቅም፣ አሀዙን ከመግለጥ ተቆጥቦአል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን አስከፊ ኑሮ እና ጭቆና ለመገላገል በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ አገር ጥለው እየተሰደዱ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ስደተኞች ሞያሌ ድንበር አካባቢ እየተተራመሱ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጧል። በግብጽ አድርገው ወደ እስራኤልና ወደ አውሮፓ ለመሄድ የሚሞክሩ ስደተኞች ደግሞ የሆድ እቃቸው እየወጣ ለገበያ እንደሚቀርብ በቅርቡ ሲኤን ኤን እና አንድ የአውስትራሊያ ቴሌቪዥን ይፋ አድርገዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤሩት ከተማ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሊባኖሳዊው ጎረምሳ ስተደበደብ የነበረችው የ33 አመቷ አለም ደቻሳ ራሱዋን ማጥፋቱዋን ተህ ዴይሊ ስታር ዘግቧል። የኢትዮጵያ ቆንስላ ሰራተኛ የሆነው አሳምነው ደበሌ አለም ራሱዋን አንቃ መግደሏን ለጋዜጣው አረጋግጧል። ወጣቷ እስካለፈው ቅዳሜ ቅዳሜ ድረስ በመልካም ሁኔታ ላይ ትገኝ እንደነበር አቶ አሳምነው ገልጠዋል።
በኢትዮጵያዊቷ ላይ የተፈጸመው ግፍ የሊባኖስን መንግስት ማስወገዙ ተከትሎ የሊባኖስ መንግስትም ይቀርታ መጠየቁ ይታወሳል።
የጋዳፊ የልጅ ሚስት የፈላ ውሀ ከደፋባባችና በሲኤን ኤን ይፋ ከሆነው ከሸዋየ ሞላ አሰቃቂ ቪዲዮ በሁዋላ፣ አለም ደቻሳ በጋጠወጡ ሊባኖሳዊ ስትደበደብ የሚያሳየው ቪዲዮ በኢትዮጵያ ሴቶች ልጆች ላይ የሚደርሰውን አሰቃቂ ግፍ አለም እንዲመለከተው የረዳ ነው።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide