በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

ኢትዮጵያውያኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመገኘት የመንግስት ወታደሮች በኦሮሞ እና በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አውግዘዋል።
የሰልፉ አስተባባሪ ከሆኑት መካከል ዶ/ር ዘውዱ ነቺሳ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የተለያዩ ጥያቄያቸውን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ክፍል አቅርበዋል። ጉዳዩን እንደሚከታተሉት ባለስልጣናቱ መግለጻቸውንና የተመድ ከፍተኛ ኮሚሽነር በተገኙበት ደብዳቤ ቀርቦላቸዋል። ኮሚሽነሩም ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉት ቃል መግባታቸውን ዶ/ር ዘውዱ ገልጸዋል
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገችው ጫልቱ ሙሃመድ በአገር ቤት የመንግስት ወታደሮች በህዝቡ ላይ የሚፈጽሙትን ግድያ ለመግለጽ ቃላት እንደሌላት ተናግራ፣ ተቃውሞዋን ለማሰማት ወደ አደባባይ መውጣቷን ተናግራለች።