በሳውድ አረቢያ በሃጅ ጸሎት ላይ በተፈጠረው አደጋ የሟቾች ቁጥር ጨመረ

መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስከረም 13 ቀን 2008 ዓም የሃጅ ጸሎት ለማድረስ ወደ አገሪቱ ከተጓዙት ኢትዮጵያውያን መካከል 47 ሙስሊሞች መሞታቸውን የእስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት አስታውቋል።
24 ጸሎት አድራሽዎች ቆስለው ከሆስፒታል ሲወጡ ፣ 2ቱ አሁንም ተኝተው በመታከም ላይ ናቸው።
በእለቱ በደረሰው አደጋ የሳውዲ መንግስት 700 ሰዎች እንደሞቱ ቢናገረም፣ በእየለቱ የሚወጣው አሃዝ የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ መሆኑን ያመለክታል። በተፈጠረው አደጋ ዙሪያ የሳውድ አረቢያ መንግስት እስካሁን ሃላፊነት አልወሰደም።