በሳውላ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደሙ

በሳውላ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደሙ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) በጎፋ ወረዳ ሳውላ ከተማ ላይ ዛሬ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።
እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፣ በደኢህዴን ባለስልጣናትና እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ለሳምንት የቆዬ ውዝግብ ነበር። ባለፈው ሳምንት ለዶ/ር አብይ የተደረገውን የድጋፍ ስልፍ ተከትሎ ህዝቡ የአካባቢውን ባለስልጣናት መቃወሙ ያስቆጣቸው የወረዳው ባለስልጣናት በወጣቶቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲዝቱ የሚያሳይ የድምጽ ማስረጃዎች ለኢሳት ደርሰው ነበር።
ወጣቶቹ- “ከዶ/ር አብይ ጎን የማይቆም ደኢህአዴን የተባለን ድርጅት አንፈልግም” በማለት ዛሬው ቭተቃውሞአቸውን ሲገልጹ እንደነበር ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልጸዋል።