በሳኡዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ሊያደርግ ነው

ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር በሚል ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2009 ዓም ይካሄዳል። ጥሪውን ያስተላለፈው በአገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሲሆን፣ ዘመዶቻቸው በግፍ የተገደሉባቸውም ሆኑ አገዛዙን የሚቃወሙት ሁሉ በኢምባሲው ተገኝተው ተቃውሞአቸውን እንዲያሰሙ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።