ሐምሌ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በጥንቃቄ የመረጣቸው የሲዳማ ተወላጆች በዛሬው እለት በሲዳማ ባህል አዳራሽ ተሰብስበው የክልሉ መንግስት ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ህዝቡ እንዲጠይቅ አደርገዋል።
12 ጥያቄዎች ለባለስልጣናት የቀረቡ ሲሆን፣ አቶ ሽፈራው ” የሲዳማን ጥያቄ አሁን ለማቅረብ እንደማይቻል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሽሎአቸው ወደ ስራ ሲመለሱ እንደሚያቀርቡት ተናግረዋል።
በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ፣ የስብሰባውን አካሄድ ለመቃወም የሞከሩም ነበሩ።
አዋጅ አዋጅ የሚል ርእስ አለው ወረቀት ዛሬ በአዋሳ ሲበተን እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጧል።
ዛሬ በተበተነው ወረቀት ላይ ” ጊዜው ወደ መጨረሻው በመቃረቡ ይህንን ትውልድ ገዳይና ዘር ጨራሽ አፈናና እጅ አዙር አገዛዝ ሁከት በሌለበት በሰለጠነ መንገድ አንድ ላይ በመሆን ” እንቃወመው የሚል መልክት ተላልፎአል።
ኢሳት ባለፈው ሳምንት ዛሬ በሲዳማ በሀል አዳራሽ ስብሰባ እንደሚካሄድ ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide