ጥቅምት ፲፭ (አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያኑ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የሱዳን መንግስት ኢትዮጵያውያንን በዘፈቀደ እያሰረ ከፍተኛ ገንዘብ ይቀበላል። ከኢህአዴግ የደህንነት አባላት ጋር በመነጋገርም፣ ገዢውን ፓርቲ ይቃወማሉ የተባሉትን እያፈነ ወደ ኢትዮጵያ ይልካል።
ፍትህ አጥተን እየተሰቃየን ነው የሚሉት ኢትዮጵያውያን ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ቢሆንም፣ ድምጻቸውን የሚያሰማላቸው አካል ማጣታቸውን ገልጸዋል።