ጥቅምት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለህዳሴ ግድብ ማሰሪያ ከሰራተኛው የተሰበሰበ ከ 35,ሺ ብር በላይ ተዘረፈ::
ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው መስሪያ ቤቱ የተዘረፈውን ገንዘብ ከመንግስት ካዘና ወጪ በማድረግ ለመሙላት ሞክሯል፡፡
እስካሁን ድረስ ከመስሪያቤቱ በተለያዩ ጊዜያት ከ245, ሺ ብር በላይ የተሰረቀ ሲሆን ጉዳዩ እንዲጣራ ያዘዙ የስራ ሃላፊ በሰበብ አስባቡ ከሃላፊነታቸው እየተነሱ ነው፡፡
ገንዘቡን ዘርፈዋል የተባሉት ግለሰብ በዋስ ከተለቀቁ 5 ወራት ቢሆናቸውም እስከአሁን ድረስ ምንም ክስ አልተመሰረተባቸውም፡፡ ቢሮው አሁንም ድረስ እንደታሸገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎአል፡፡
በጎዳና ተዳዳሪዎች ስበብ የተመደበ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ መሰረቁ የታወቀ ቢሆንም መንግስት እስካሁን እርምጃ አለመውሰዱንም መረጃውን ያደረሱን ሰራተኞች ገልጠዋል።