ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008)
በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ውስጥ የህወሃት ታጣቂዎች በአካባቢው የሚኖሩ ገበሬዎችን እየገደሉ፣ እያሳደዱና፣ ዝርፊያ እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመለከቱ።
ከሶስት ቀን በፊት ማለትም ሚያዚያ 3 ፥ 2008 ላይ አርማጭሆ ኩርቢት በተባለ ቦታ ተሰማርተው የነበሩ የህወሃት ታጣቂዎች አንድ ገበሬ ገድለው ንብረታቸውን እንደዘረፏቸው የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙ የህወሃት ታጣቂዎች ተቃዋሚዎችን በተለይም አርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ናቸው ብለው በጠረጠሯቸው ሰዎች ላይ የግድያና የዝርፊያ ተግባር እንደሚፈጽሙባቸውም ተመልክቷል። ትክል ድንጋይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ም አለመረጋጋት እየታየ ሲሆን፣ የ መከላከያ ሰራዊት ምክንያቱ ባልታወቀበት ሁኔታ በአካባቢው በብዛት ተሰማርቶ እንደሚገኝም መረዳት ተችሏል።