ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርበኞች ግንቦት7 ስር ታቅፈው እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹት ታጋዮቹ ፣ ህወሃት ለአንድ አርበኛ ታጋይ 400 ያክል ወታደሮችን አሰልፎ ታጋዮቹን ለመፈለግ በሚያደርገው ዘመቻ አርሶአደሩ እየተያዘ እስር ቤት በመወርወሩ እርሻ አልታረሰም።
“ አንድ ሰኔ የነቀለውን 10 ሰኔ አይተካውም “ የሚሉት ታጋዩ፣ “ከማረሻ ውጭ ምን አለን? ማረሻ ከተሰቀለ፣ ቀንበር ከተሰቀለ፣ ጅራፍ ከተሰቀለ ከዚህ ውጭ ምን አለ? ሁላችንም ማረሻችንን፣ አካፋችንንና ዶማችንን ይዘን ወደ ትግል እንዙር” ይላሉ
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በአካባቢው ተሰማርተው፣ ህዝቡን እያሰሩና እያሰቃዩ ነው። አፈናው ከሌሊቱ 7 ሰአት እንደሚጀመር የሚገልጹት ታጋዮች ፣ ደሳለኝ ወልዴ እሸቴ የተባለ የህክምና ባለሙያ በሌሊት ተወስዷል ብለዋል።
“የእኛ ቤተሰቦች ከታሰሩ ከ4 ወይም 5 ወራት በላይ አስቆጥሯል” የሚሉት ታጋዩ፣ እጃቸው የተሰበረ፣ አይናቸው የጠፋና ጥርሳቸው የረገፈ በርካቶች መሆናቸውን ገልጸው፣ ህዝቡ ከዚህ ጥቃት ለመከላከል አድራሻውን እያጠፋ ነው።
“ለመሆኑ አርበኞች ግንቦት7 ድጋፍ ያደርግላችሁዋል ወይ ? ህዝቡስ ከእናተ ጋር ነው ወይ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ህዝቡ ጥቃቱ ቢበረታበትም ታጋዮችን ከመቀላለቀል ወደ ሁዋላ አለማለቱን እንዲሁም ከድርጅታቸው ድጋፍ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።