በሰሜን ጎንደር በማንኛውም ጊዜ ግጭት ሊነሳ ይችላል ሲሉ ነዋሪዎች አስጠነቀቁ

ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ ፈጥሮታል በሚባለው በአማራና ቅማንት የሰሜን ጎንደር ተወላጆች መካከል ያለው ግጭት ለጊዜው ጋብ ያለ ቢመስልም፣ ድጋሜ ግጭት ለማስነሳት ውስጥ ለውስጥ የቅስቀሳ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
አንዱ በሌላው ላይ የሚያካሂደው የማጥላላት ዘመቻ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በዚሁ የቅስቀሳ ስራ ላይ የኢህአዴግ ሹሞች ሙሉ በሙሉ እጃቸውን ማስገባታቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገለጹት ከዛሬ ነገ ግጭት ይንሳል በሚል ስጋት የተረጋጋ ህይወት ለመምራት አልቻሉም።
በአንዳንድ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ከተዘጉ ወራትን ቢያስቆጥሩም ሊከፈቱ አልቻሉም።