ጥር ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ወሎ ትናንት ጥር 24 2009 ዓም በዞኑ ጽቤቶች የጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባ የተጠራ ሲሆን፣ ሰራተኞችና አመራሩ መስማማት ሳይቸሉ ቀርተዋል ። አመራሩ “በሀገሪቲ በዚህ ደረጃ ለሚታየው ውድቀት ተጠያቂው ሲቪል ሰርቪሱ “ ሲል፣ ሰራተኛው ደግሞ ለውድቀቱ ተጠያቄው ሲቪል ሰርቪሱ ሳይሆን አመራሩ ነው “ በማለት ተከራክሯል።
ሰራተኛውን ካስገረሙት ሹመቶች መካከል የዞን ማህበራት ሃላፊ ሆና የተሾመችው ግለሰብ የዞኑ ፎቶ ኮፒ ሰራተኛ ሆና ስታገለግል የነበረች መሆኗ ነው ። ከዚህ ቀደምም በወልዲያ ጤና ጣቢያ ፅዳት ሰራተኛ የነበረች ግለሰብ፣ የወልድያ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ፅቤት ምክትል ሀላፊ ሆና ተሹማ ነበር ። ተሻሚዎቹ ራሳቸውን በትምህርት አሻሽለው ያገኙት ቦታ አለመሆኑን የሚጠቅሱት ምንጮች፣ በፓርቲ አባልነታቸውንና ሰራተኞችን እንዲሰልሉ ተብለው መሾማቸውን ይናገራሉ።