(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 16/2010) በሰሜን ኮሪያ የኒዩክለር ሙከራ ጣቢያ ውስጥ ከባድ ፍንዳታ መከሰቱ ተሰማ።
ሰሜን ኮሪያ የሙከራ ጣቢያውን ከጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሚል መዝጋቷን አስታውቃ ነበር።
ከደቡብ ኮሪያና ከአሜሪካ ጋር የተጀመረውን ድርድር ተከትሎ ነው ከወራት በፊት ሰሜን ኮሪያ ያላትን የኒኩለር ጦር መሳሪያ እንደምትቀንስ አስታውቃ የነበረው።
በአሜሪካ በኩል ከኒዩክለር መሳሪያዎቼ ጋር በተያያዛ የአስገዳጅነት ሁኔታን ስለታዘብኩ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጋር ለመገናኘት ያለኝን እቅድ ልሰርዝ እችላለሁ ስትልም ያስጠነቀቀችው በዚህ ሰሞን ነበር።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው እንግዲህ ዛሬ ላይየሰሜን ኮሪያ የኒኩለር ሙከራ ጣቢያው ውስጥ ከባድ ፍንዳታ ተሰማ የተባለው።
ከሰሜን ኮሪያ መንግስት ፈቃድ የተሰጣቸው ጋዜጠኞች ብቻ እንዲታዘቡት በተደረገው በዚህ የኒኩለር ሙከራ ጣቢያ ፍንዳታ በትክክልም 3 ከፍተኛ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብሏል በዘገባው።
ሰሜን ኮሪያ ከሁለቱ ሃገራት ጋአ የጀመረችውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተከትሎም በኒዩክለር ሙከራ ጣቢያው የምታካሂደውን ስራ መቀነሷን አስታውቃ ነበር።
በድንገት የተከሰተው የአሁኑ ፍንዳታና መንስኤው ግን በግልጽ አልተቀመጠም።