በርካታ የኦሮሞ አባቶች በሶደሬ የመዝነኛ ማእከል መሰብሰባቸው ታወቀ ክልሉን አረጋጉ ተብለዋል

ነሃሴ  ( ሃያ አምስ ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- ኦህዴድ ክልሉን ያረጋጉልኛል ያላቸውን በርካታ ቁጥር ያላቸውን የኦሮሞ አባቶች በመጥራት በሶደሬ የመዝናኛ ማእከል ስብሰባ እያደረገ ሲሆን፣ ከሆቴሉ ምንጮች በተገኘው መረጃ ለአንድ አልጋ በቀን ከ700 እስከ 1 ሺ ብር ይከፈላል። ነሃሴ 23 ቀን ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በመቱ ዩኒቨርስቲ አውቶቡሶች ተጭነው የመጡት አባቶች፣ ለ4 ቀናት የሚቆዩ ሲሆን፣ 6 በሬዎች ለእርድ እንደቀረቡላቸው ታውቋል።

አባቶቹ ወደ የአካባቢያቸው ሲመለሱ የአካባቢውን ወጣቶች እንዲመክሩና ክልሉን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት ይሰጣቸዋል።