ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ወኪላችን እንዳለው ባለፈው ቅዳሜ ህወሃት ለኢህአዴግ ጉባኤተኞች ባዘጋጀው የእራት ግብዣ፣ ከ2 ሺ ያላነሰ ሰው ተገኝቷል። ለእንግዶቹ የተለያዩ ምግቦች፣ ቁርጥ ስጋ እና ውስኪ እንደ ልብ ቀርቦላቸዋል።
ግብዣው የተደረገው 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የሚላስና የሚቀመስ እንደሌለው ሪፖርት በተደረገበት ወቅት ነው። በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ድርቅ መግባቱን ሪፖርቶች ያስረዳሉ።
ኢህአዴግ ለተለያዩ በአላት ግብዣዎች በእየአመቱ በቢሊዮን የሚጠጋ ብር ያወጣል። በሌላ በኩል ኢህአዴግ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን በድጋሜ ሊቀመንበር፣ አቶ ደመቀ መኮንንን ደግሞ ም/ል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
በሌላ በኩል አቶ ሃይለማርያም በሰቆጣ የአሸንዳን በአል ለማክበር የሚገኙ ሲሆን፣ በአሉ ካለፈ ቀናት ቢቆጠሩም፣ ሴቶች ለበአሉ ሲባል ሹሩባቸውን እንዳይፈቱ ታዘዋል።
በአሉ የሚከበረው በከተማው ውስጥ በድርቁ ምክንያት ውሃ በጠፋበት እና በርካታ ህዝብ ” በጭንቀት ተውጦ በሚገኝበት ወቅት ነው። የአቶ ሃይለምርያም ጉብኝት በአካባቢው ድርቅ አለመግባቱን ለማሳየት ተብሎ የተዘጋጀ ነው። ይሁን እንጅ ኢሳት በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ ችጋር መከሰቱን ከነዋሪዎች አንደበት ለማረጋገጥ ችሏል። ይህንን በተመለከተ ያጣነቀረውን ዘገባ ነገ ያቀርበዋል።