በርካታ የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወታደሮች ተደብድበው ሆስፒታል ተኝተዋል
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሚያዚያ 3 ቀን 2010 ዓም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ተማሪዎች በመኝታ ክፋል በማምራት ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ በመፈጸማቸው በርካታ ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ሃረማያ ሆስፒታል ተኝተዋል።
ተማሪዎቹ የታሰሩ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ወታደሮች “ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳ መሰላችሁ?” በማለት ወደ ክፍላቸው እየገቡ እንደቀጠቀጡዋቸው ወኪላችን ገልጿል።
ተማሪዎቹ ትምህርት ጀምረው የነበረ ቢሆንም፣ የታሰሩ ተማሪዎች ሳይፈቱ በመቅረታቸው እንደገና ትምህርት ማቋረጣቸውን ተከትሎ ነው እርምጃው የተወሰደባቸው።