በርካታ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎች እየታሰሩ እየተገደሉና እየተዋከቡ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2011 እስካሁን ያለውን ሁኔታ አጥንቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ፣ ከ5 ሺ ያላነሱ ኦሮሞች በእስር ላይ ይገኛሉ። ጥናቱን ያጠኑት የአምነስቲ የኢትዮጵያ ክፍል ሃላፊ ክሌር ቤስተን መንግስት አገሪቱን

ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን፣ ለአለማቀፍ የሰብአዊ  መብት ድርጅቶች እንዲሁም ለአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ክፍት ቢያደርግ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከዚህም ሊልቅ ይችላል ሲሉ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ዶ/ር  መረራ ጉዲና በአምነስቲ የተጠቀሰው ቁጥር አንሷል ይላሉ፣ ዶ/ር መረራ በአምቦና በወለጋ ብቻ ከአምስት ሺ በላይ አባላት ታስረዋል ይላሉ።