ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ጌታቸው መኮንን መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ1 አመት ከ8 ወራት ላላነሰ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙት 16 ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣
ከእነሱ መካከል አቶ አግባው ሰጠኝ በማንነቱ የተነሳ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ገልጿል።
አቶ አግባው ከግንቦት 17 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በቂሊንጦ ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን፣ በጀመረው የረሃብ አድማ ለአንድ ሳምንት ያክል ምግብ አለመመገቡ ታውቋል።
አግባው አማራ በመሆኔ በደል እየተፈጸመብኝ ነው ያለ ሲሆን፣ የእስር ቤቱ ሃላፊዎች “ ዘረኛ ብለህናል” በማለት እያሰቃዩት መሆኑን ገልጿል። አግባው በፍርድ ቤቱ ፊት “ ዘረኛነታችሁ ሀቅ ነው” ሲል ተናግሯል።
16 ተከሳሾች ናቸው። ከታሰሩ 1 አመት ከ 8 ወር ሆናቸው። ዛሬ ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ በሚለው ላይ ይወስናሉ ቢባልም አልደረሰም በሚል ለሰኔ 21 ቀጠሮ ተሰጣቸው። ተከሳሾች ሁሉም ከአማራ ክልል
የመጡ ናቸው። የፓርቲዎች የዞን አመራሮች ነበሩ። በተለያየ ጊዜ በማንነታቸው ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤት ተናግረዋል።
አካላዊ ጉስቁልና የከፍተኛ የሰውነት መደካም የሚታይበት አግባው “ ቤተሰቤንና ጠበቃዬን እንዳላይ ካልተደረገ በረሃብ አድማው እቀጥልበታለሁ፣ ቀጣይ ቀጠሮ ላይ ሬሳዬ ሊመጣ ይችላል” ብሎአል።
16ቱ ተከሳሾች ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ በሚለው ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኛሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔው አልደረሰም በሚል ለሰኔ 21 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሁለቱም ተከሳሾች የሰማያዊ እና የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የአካባቢ አመራሮች የነበሩ ናቸው።