በሞያሌ ለተነሳው ግጭት ተጠያቂ የተደረጉ ተፈረደባቸው

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት አመት በኦሮምያና በሶማሊ ክልሎች የድንበር ከተሞች የተነሳውን ግጭት መርተዋል የተባሉና ቁጥራቸው በውል ላልታወቀ

ዜጎች ሞትና ለንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የሞያሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች 29 ሰዎች እስከ 19 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

21 ተከሳሾች በሌሉበት ሲወሰንባቸው የሞያሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጉዩ ዋርየን በ14 አመት፣ ዳማ ዱዮን የተባሉት ደግሞ በ19 አመት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

ሞያሌ ከተማ ግማሹ በኦሮምያ ቀሪው ደግሞ በሶማሊ ክልል ይተዳደራል። በአካባቢው በተደጋጋሚ በሚነሳ ግጭት የበርካታ ዜጎች ህይወት በተደጋጋሚ ያልፋል።