በሞቃዲሹ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ደረሰ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንዳደረሰው በሚገመተው የአጥፍቶ መጥፋት እርምጃ 12 የጸጥታ ሃኢሎች መገደላቸው ታውቋል። ጥቃቱ የጸጥታ ሃይሎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ባለፈው ሳምንት በፕሬዚዳንቱ ግቢ ውስጥ በደረሰ ጥቃት የሶማሊያ መንግስት ነባር የአመራር አባላት መገደላቸው ይታወሳል። አልሸባብ ከአፍሪካ አገራት በደረሰበት ጥቃት ሞቃዲሹን ለቆ ቢወጣም፣ በተደጋጋሚ እየወሰደ ባለው የፈንጅ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው።