ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008)
በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለማሰማት አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በወሰዱት የተኩስ ዕርምጃ በትንሹ አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን እማኞች ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል።
ይኸው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በትክክል ሊታወቅ ያልቻለ ነዋሪዎች ለእስር መዳረጋቸውን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።