በምስራቅ ሸዋ ቢሾፍቱ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

ኢሳት (መጋቢት 23 ፥ 2008)

ሃሙስ በምስራቅ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ የደረሰውን የቦንብ አደጋ ተከትሎ አርብ በከተማ ተቃውሞ በመቅረብ ላይ መሆኑም ታውቋል።

በከተማዋ ያልተለመደ የጸጥታ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ የሚናገሩት ነዋሪዎች የመንግስት አካላት ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በክልሉ እየተካሄደ ካለው ተቃውሞ ጋር በተገኛኘ በዩኒቨርስቲዎችና በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ የቦንብ ጥቃቶች ሲደርሱ መቆየታቸው ይታወሳል።