በምስራቅ ሀረርጌ የተከሰተው ረሃብ የህልውና ስጋት መደቀኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል

ጥር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ረሃብ ገብቷል የሚሉት ነዋሪዎች፣ አስቸኳይ እርዳታ በፍጥነት ካልደረሰላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ሊያልቅ ይችላል። በገጠር አካባቢ የሚኖረው ህዝብ ወደ ከተሞች መሰደድ ጀምሯል። ምንጮችና ወንዞች በመድረቃቸው ውሃ ለማግኘት አልተቻለም ሲሉ የውሃ እጥረት ለመሰደዳቸው ዋና ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
አንዳንድ አርሶአደሮች ከብቶቻቸውን እየሸጡ ችግሩን ለማሳለፍ እየሞከሩ ቢሆኑም፣ የከብቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ በርካሽ ለመሸጥ ተገደዋል።
በዚህ አመት ከ10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።