ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቦንኬ ወረዳ ላታ ቀበሌ ከታሰሩት
9 አርሶደአሮች መካከል 3ቱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። አዳነ
አለማየሁ፣ አስኔ አለማየሁ፣ ክልክሌ አባ፣ ልልቱ ኮዳ፣ አይማ ዳዳ፣ ጋላሂ ጋሞ፣ ዳንኤል ጉዳ፣ አብሌ
አለማየሁ እና አባተ እንዳለ የተባሉት አርሶአደሮች “ተጨማሪ ማዳበሪያ አንፈልግም ቀድሞ
ለወሰድነውም እዳችንን ለመክፈል አልቻልንም” በማለታቸው መታሰራቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ሙና ሄና፣ ካንጅራ ካርቁራ፣ ካላ ጎሜ፣ ካሲሲ ጎሬ፣ ዳዊት ጉቴ፣ ባባ በዛብህ እና ጎኒሳ ጎበዜ የተባሉት
ደግሞ እየተፈለጉ ነው።የማዳበሪያ እዳቸውን ለመክፈል ያልቻሉ ሌሎች የወረዳዋ አርሶደአሮችም
እየተዋከቡ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው መኩራ አልተሳካም።