በማንችሰትር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ የሚፈጸመው ግድያና አፈና እንዲቆም ጠየቁ

መስከረም ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝ ማንችስተር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችን በማሰማት እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና በግፍ የተገደሉ ዜጎችን ፎቶግራፎች በመያዝ አገዛዙ በአገር ውስጥ የሚፈጸመውን ግድያና አፈና አውግዘዋል።ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ ይድነቃቸው ረዳ እንደተናገረው ቀደም ብለው ለተለያዩ የፓርላማ አባላት፣ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎች ዘንድ መልእክት መተላለፉን ገልጸዋል። የተቃውሞ ሰልፉ በቢቢሲ የሰሜን ቅርንጫፍ ክፍል ጽ/ቤት ፊት ለፊት መካሄዱን የገለጸው አቶ ይድነቃቸው፣ ቢቢሲ ገልለተኛ እና ሰፋት ያለው ዘገባ እንዲያቀርብ መጠየቃቸውንም ገልጿል ።