በሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ ፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ::

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ የፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ::

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ ገብቶል በማለት ያነሱት ተቃውሞ አመት ማስቆጠሩን ያስታወሰው የፊርማ ማሰባሰብ መግለጫ በአሰሳ አርሲና በገርባ በመንግስት ታጣቂዎች 7 ሰዎች መገደላቸውን ፡በረካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ሌሎች መሰደዳቸውን በመግለጽ የተባበሩት መንግስታት የሀይማኖት ነጻነት ቢሮ የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ እንዲጽፍ በመጠየቅ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል::

ኢትዮጵያ የአለም አቀፉን የሰብአዊ መብትና የሲቪልና የፖለቲካ መብቶችን ለማክበር ተስማምታ የፈረመች አገር መሆኖን ያስታወቀውና የፊርማ ማሰባሰቡን የጠየቀው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመጅሊስ አባሉን በመስኪድ እመርጣለሁ እያለ መንግስት በቀበሌ አስመርጧል ካለ በሆላ ይህም በሀይማኖት ጣልቃ መግባት በመሆኑ መንግስት ከተግባሩ እንዲታቀብና የሀይማኖት ነጻነት እንዲያከብር የተባበሩት መንግስታትን ለመጠየቅ ማ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎል::