በመላ አገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት መክፋቱ ተነገረ::

ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:-  የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት እና የገንዘብ ሚኒሰትሩ አቶ ሶፍያን አህመድ  የዋጋ ንረቱ እየወረደ ነው በማለት በተናገሩ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዋጋዎች እንደገና ወደ ላይ እየወጡ ነው። የእህል ዋጋ በከፍተና ፍጥነት እየጨመረ ሲሆን አንዳንድ የፍጆታ እቃዎችም ከገበያ እየጠፉ ነው። ዘይት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዋና ከተማዋም ሆነ በክልል ከተሞች ጠፍቷል። ምግብ ቤቶች ዘይት በማጣት ስራቸውን እያቆሙ ነው።

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው ” የኑሮ ውድነቱ ህዝቡን ጎዳው ከማለት ሙሉ በሙሉ ግጦ በላው ማለት ይሻላል በማለት ለዘጋቢያችን ተናግረዋል።

አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት ባለሀብቶች ከአቶ መለስ ህመም ጋር ተያይዞ  ሀብታቸውን ማሸሽ መጀመራቸው የኑሮ ውድነቱን ሳያባብሰው አልቀረም። አንዳንድ ነጋዴዎችም ነገ የሚሆነው አይታወቅም በማለት ከውጭ ያስመጧቸውን እቃዎች ለመሸጥ ፈቃደኛ አልሆኑም እየተባለ ነው፡፤ በዚሁ መሀል ህብረተሰቡ በኑሮ ውድነቱ እጅግ እየተጎዳ ነው በማለት ዘጋቢአችን ገልጧል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide