በሕንድ አቧራን የቀላቀለው አውሎ ንፋስ የ100 ሰዎችን ሕይወት አጠፋ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2010)በሕንድ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተው አቧራን የቀላቀለው አውሎ ንፋስ የ100 ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።

በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ያሉ ከተሞችን መታ የተባለው ይሄ አውሎ ንፋስ ሰዎች በተኙበት መከሰቱ ደግሞ አደጋውን የከፋ አድርጎታል ተብሏል።

አቧራ የቀላቀለው አውሎ ንፋስ ቤቶችን አፍርሷል፣የኤሌክትሪክ አገልግሎትን አቋርጧ ሌሎች ጉዳቶችንም አድርሷል ብሏል ዘገባው።

በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት አውሎ ንፋስ እንደሚከሰት ቢታወቅም በዚህን ያህል ደረጃ የሰው ሕይወትን ሲያጠፋ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

በህንድ ሰሜናዊ ግዛት ይህንን መሰል አቧራ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ሲከሰት የመጀመሪያው አይደለም ይላል ቢቢሲ ዘገባውን ሲጀምር።

ነገር ግን የሰው ሕይወትን በዚህን ያህል ደረጃ ሲያጠፋ ግን የመጀመሪያው ነው ብሏል ዘገባ።

አቧራ በቀላቀልው በዚህ አውሎ ንፋስ ኡታር ፓራዲሽ በተባለጽ ቦታ ብቻ 64 ሰዎች ሲሞቱ የታጂመሀል መገኛ በሆነችው አግራ ግዛትደግሞ 43 ሰዎች ሕይወታቸውን አተዋል። የሟቾቹ ቁጥር አሁን ላይ እየወጣ ካለው 107 ሰዎች በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል።

በአደጋው የዚህን ያህል ሰው ሕይወት ሊያልፍ የቻለውም ሰዎች በተኙበት በመከሰቱ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

በአካባቢው የሚገኙት ቤቶች በጭቃ የተሰሩ መሆናቸው ደግሞ ለቤቶቹ መፍረስና  ለሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል ተብሏል።

በአካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተቋርጧል፣ዛፎች ወድቀዋል፣የቤት ውስጥ የቤት እንስሳት አልቀዋል በአጠቃላይ አደጋው ብዙ ንብረቶችን አውድሟል ሲል ዘገባው አስፍሯል።

የኡታር ፓራዲሽ አስተዳደር ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች እስከ 400,000 ሩፔ ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል።

ባለፈው ሚያዚያ የ19 ሰዎች ሕይወትን የቀጠፈ አደጋ የተከሰተ ቢሆንም በ25 አመታት ታሪክ ውስጥ ግን እንደዚህ አይነት የከፋ አደጋ ሲያጋጥም የመጀመሪያው ነው ተብሏል።