ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- እርሳቸውና ከርሳቸው ጋር የሚገኙ ጳጳሳትም ይህንኑ ኃላፊነታቸውንለመወጣት እየሰሩ መሆናቸውን አመለከቱ::
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት የ2005 ዓ.ም.የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በማስመልከት በጽሁፍ ባሰራጩት መልዕክትነው::
አቡነ መርቆርዮስ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ካከበሩበት ከካናዳ ቶሮንቶባስተላለፉት መልዕክት መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚያግድ ምንምዓይነት ችግር እንደሌለባቸው አመልክተዋል:: ስልጣንና ክብርን እንደማይሹያብራሩት ብጹዕ አቡነ መርቆርዮስ ሆኖም የልዩነቱ ምዕራፍ ተዘግቶ አንድ እረኛያላት አንዲት ቤ/ክ ለትውልድ መተላለፍ እንዳለበትም አስገንዝበዋል::ሲቀጥሉም “አሁን በኛ በኩል ሕገ-ቤ/ክርስቲያን የሚያስከብርና ቤ/ክርስቲያንንበሰላምና በአንድነት የሚያጸና ሰላም እንዲመጣ ለቤ/ክ ሰላም እና አንድነትቅድሚያ ሰጥተን እየሰራን ነው” ሲሉ አመልክተዋል::
ሰላም የሚመጣው ሁሉም ለሰላም የበኩሉን አስተዋዕጾ ሲያደርግ ነው ያሉትብጹዕ አቡነ መርቆርዮስ በአገር ላሉት አባቶች ጥሪ አቅርበው በነርሱ በኩልለሰላም ያለውን ዝግጅት አስፍረዋል::
“በኢትዮጵያ ያሉት ወገኖቻችን ሊቃነ ጳጳሳትም ቢያስቡበትና መልካምየሆነውን ነገር ለማድረግ ቢስማሙ ለቤ/ክርስቲያናችን አንድነት ጠቃሚ ነው”በማለት ያስገነዘቡት ፓትሪያርክ መርቆርዮስ “ያ ካልሆነ እግዚአብሔር ባኖረንእየኖርን በአለም የተበተነውን ሕዝባችንን እያጽናናንና እየባረክንየእግዚአብሔርን ቀንና ጊዜ እንጠብቃለን::በኛ በኩል መቼም ቢሆን ከቤ/ክሰላምና አንድነት የምናስቀድመው አንዲት ነገር የለም” በማለት መልዕክታቸውንአስተላልፈዋል::