(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በላዎስ በመገንባት ላይ ያለ አንድ ግድብ በድንገት ፈርሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተሰማ።
ለኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫነት የተገነባው ይህ ግድብ 770 ሜትር ርዝመት እንዲሁም 16 ሜትር ከፍታ እንደነበረው ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።
በፈረንጆቹ 2013 ግንባታው የተጀመረው ይህ ግድብ ለመደርመሱ ምክንያት የሆነውም በአካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ መሆኑም ተመልክቷል።
ከጣለው ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞም ከ6,600 በላይ ሰዎች ቤት አልባ መሆናቸው ተዘግቧዋል።