ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ዞን በከምሴ ከተማ ባለፈው ሳምንት በተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ወደ የመን እና እና ሳውድ ኣረቢያ በህገ ወጥ ዝውውር ከሚጓዙ ወጣቶች ጀርባ ደህንነቶችና የፖሊስ ሃይሎች መኖራቸው ተመልክቷል።
የዞኑ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት እንድሪያስ አሊ ሸቱ ለኢሳት እንደተናገሩት የህገወጥ ዝውውሩ ችግር አገራዊ ይዘት ያለው ቢሆንም በህገወጥ ዝውውሩ ላይ እየተሳተፉ በሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች ላይ አስፋለጊው እርምጃ መወሰድ መጀመሩን ተናግረዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች በዚሁ ከህዝብ ጋር እርቅ ለማውረድ በሚል ኣላማ በተጠራ ስብሰባ ላይ የፖሊስ ስርዓት አልበኝነት እየጨመረ መምጣቱን በፖሊስ በከፋ ሁኔታ እየተደበደቡ ክብረ ነክ ነገሮች እየተፈጸመባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት ከ እስልምና ጋር ተያይዞ በሰላም የኖርባትን ሃገር አሸባሪ በሚል ስያሜ ዙሪያውን ጨለማ እንዳደረገባቸውና ተሸማቀው እንዲኖሩ አንዳስገደዳቸው ነዋረዎች ተናግረዋል
የጸጥታ ዝርፍ ሀላፊው በበኩላቸው ከዚህ በፊት የነበረው ችግር ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲተያይ የተሻለ መሆኑን ገልጻዋል። በከሚሴ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑንም ተናግረዋል