በሃዋሳ በድጋሜ ግጭት ተነሳ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም) በአመታዊው የሲዳማ የዘመን መለወጫ በአል -ጨምበለላ ቀን የተጀመረው ግጭት ዛሬ በድጋሜ ማገርሸቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የዛሬው ግጭት-ሁለት ሰዎች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸውን ተከትሎ የተነሳ ነው። የጨምበለላን በአል ወደ ብሄር ግጭት ለመቀየር የሚደረገውን ሙከራ ለማስቆም የአገር ሽማግሌዎች አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። ደኢህዴን ከህወሃት ጋር ሆኖ ያቀናበረው ግጭት ነው የሚሉ ነዋሪዎች፣ ግጭቱን ለማስቆም ጥረት እየተደረገ ነው ይላሉ።