በሃረር የዳቦ ዋጋ በእጥፍ ጨመረ

በሃረር የዳቦ ዋጋ በእጥፍ ጨመረ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በከተማው የሚታየው የኑሮ ውድነት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ህዝቡ ህይወቱን ለመምራት ተቸግሯል። ሰሞኑን ስንዴ ጠፋ በሚል አንድ ብር ይሸጥ የነበረው ዳቦ፣ መቶ በመቶ ጨምሮ 2 ብር መግባቱን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የዳቦው መጠንም በከፍተኛ ሁኔታ ማነሱን ይናገራሉ። አብዛኛው የመንግስት ሰራተኞችም ሆኑ አንስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በየቀኑ የሚንረውን የዋጋ ውድነት መቋቋም እንዳልቻሉ ይገልጻሉ።
የስጋ ዋጋም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። አንድ ኪሎ ስጋ 300 ብር እየተሸጠ አንስተኛ ክፍያ የሚያገኙ የመንግስት ሰራተኞች ልጆቻቸውን እንዴት ስጋ ሊያበሉ ይችላል ሲሉ የሚጠይቁት ነዋሪዎች፣ ጭማሪው ከምግብ ሸቀጦች በተጨማሪ በግንባታ እቃዎችና በቤተ እቃዎች ላይ ጎልቶ እንደሚታይ አስረድተዋል።