ቃሊቲ አካባቢ በተፈጠረው የቡድን ጸብ ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ያለፉትን 3 ቀናት በፍርሀት ቤቱ ውስጥ ለማሳለፍ ተገደደ

ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ልዩ ቦታው ሳሎ ጊዮርጊስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ በተፈጠረው የቡድን ጸብ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደልባቸው ወጥተው ስራ ለመስራት ተቸግረዋል።

ባለፉት 2 ቀናት ጸቡ በመባባሱ አንድ ወጣት በቤቱ ውስጥ በሽጉጥ ተመትቶ መሞቱን ለማወቅ ተችሎአል። እናቶች ከመጨነቃቸው የተነሳ ወጣት ልጆቻቸውን መደበቃቸውም ታውቋል።

ፖሊስ የቤት ለቤት ፍተሻ መጀመሩ ቢነገርም እስካሁን ድረስ ችግሩን ባለመፍታቱ የአካባቢው ነዋሪ  ተረጋግቶ ስራ ለመስራት አለመቻሉ ታውቋል።