(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010)
የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አመራር ቀለብ ስዮም ከእስር ተፈታች።
ሀምሌ 2 ቀን 2007 ወደ እስር ቤት ተወርውራ የነበረችው ቀለብ ስዩም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈባትን ውሳኔ በመቃወም ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረበችው ይግባኝ መሠረት 4 ዓመት በእስር እንድትቆይ ተላልፎ የነበረው የእስር ቅጣት ተቀንሶ ወደ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር ወርዶ ነበር።
በዚሁ መሰረት ቀለብ ስዩም የእስር ጊዜዋን ጨርሳ ዛሬ ከእስር ቤት ተፈታለች።