ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፒተር ስዋይዘር የተባሉ ጸሃፊ በቅርቡ በሚያሳትሙት መጽሃፍ ላይ ሼክ አላሙዲን ለክሊንተን ፋውንዴሽን 20 ሚሊዮን ዶላር እኤአ በ2006 መስጠታቸውን አጋልጠዋል።
የሼክ አላሙዲን ድርጅት ለክሊንተን ፋውንዴሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ እርዳታው የተሰጠው በኢትዮጵያ መንግስት ስም ሲሆን፣ የቡሽ አስተዳደር የውጭ ፖሊስ በክሊንተን አስተዳደር ጊዜም እንዲቀጥል ያስስባል። በባለቤታቸው ስም ገንዘብ የተቀበሉት ሂላሪ ክሊንተን ፣
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑ በሁዋላ የአሜሪካ መንግስት በኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ማእቀብ ለመጣል ያረቀቀው ህግ እንዲሰረዝ፣ አሜሪካ ያለምንም ማንገራገር ለኢህአዴግ አስፈላጊውን እርዳታ እንድትሰጥ ማድረጋቸውን ጸሃፊው ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል።
ሼክ አላሙዲን ገንዘቡን የሰጡት ለኤድስ መከላከያ ነው ብለዋል። ሂላሪ ክሊንተን በመጪው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ይወዳደራሉ።