ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008)
የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ ሶስት የክልል ፕሬዚደንቶች በአውስትራሊያ ካንበራና ሜልበርን የጠሩዋቸው ስብሰባዎች በተቃውሞ ተበተኑ። ቅዳሜ ሰኔ 4 በካንበራ እንዲሁም ሰኔ 5 ፥ 2008 በሜልበርን የተጠራውን ስብሰባ ኢትዮጵያውያን ተደራጅተው ባስተባበሩት ተቃውሞ የተበተነ ሲሆን፣ ፖሊስ ተቃውሞውን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ለመጠቀም መገደዱን የቋጠሮ ድረገጽ አዘጋጅ ሳምሶን አስፋው ከስፍራው ዘግቧል።
የትግራይ ክልል ፕሬዜደንት አቶ አባይ ወልዱ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜደንት አቶ ሙክታር ከድር፣ እንዲሁም የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ መሃመድ በጋራ የጠሩትና የተበተነውን ስብሰባ የተመለከተ ዘገባ በቋጠሮ በተሰኘ ድረገጽ ይገኛል።