ሚያዚያ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንደገለጹት፣ ስዊድን እንደ ኖርዌይ ሁሉ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ያለገኙትን ከሰኔ ወር መግቢያ ጀምሮ ለማስወጣት ማቀዷን የኢትዮጵያን የስደተኞች ሊቀመንበር አቶ ኤፍሬም አክሊሉ ተናግረዋል።
ከአገር ተገፍቶ የወጣው ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ወረቀት ሳያገኝ፣ መንግስት ሁሉንም ሰነዶች አዘግጅቶ የሚልክላቸው እኛን ለመሰለል ሲመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በቀላሉ እንደሚያገኙ ተናግረዋል። ይህንን ለመቃወም በነገው እለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልጸዋል።