ሚያዝያ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነታቸው ያልታወቁት ሟቾች አስከሬን ማልታ ውስጥ በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ፣ የሶማሊ፣ የኤርትራና ሌሎችም አፍሪካውያን በቀብር ስነስርአቱ ላይ ተገኝተው ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
የሟቾቹ ዜግነት በውል ባይታወቅም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ ኤርትራውያን፣ ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያንና ሌሎች አፍሪካውያን ይገኙበታል።