ሰማያዊ ፓርቲና አረና ትግራይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)ሰማያዊ ፓርቲና አረና ትግራይ ሰላማዊ ሰልፎች መጥራታቸው ተገለጸ።

ሰማያዊ በአዲስ አበባ፣ አረና ደግሞ በመቀሌ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድና ቅዳሜ የሚካሄዱ ናቸው።

የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ ለኢሳት እንደገልጹት ‘’ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት” በሚል ርዕስ የተጠራው ሰልፍ እሁድ ጥቅምት 26/2010 በመስቀል አደባባይ ለተጠራው ሰልፍ የማሳወቂያ ደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ቀርቧል።

በህጉ መሰረት የማሳወቅ ግዴታው መከናወኑን የጠቀሱት አቶ ጌታነህ እሁድ የተቃውሞ ሰልፉን እናካሂዳለን ብለዋል።

አረና ትግራይ በበኩሉ በተለያዩ አካባቢዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ በመቀሌ ከተማ ቅዳሜ ሰልፍ መጥራቱን አስታውቋል።

ሁለቱንም ሰልፎች በተመለከተ በመንግስት በኩል እውቅና እስከአሁን እንዳልተሰጠው መረጃዎች ያሳያሉ።