ምእመናን የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን ከሹመት አነሱ

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-ላለፊት ሶስት አመታት የመልካም አስተዳደር ችግር ፤የፍትህ እጦት እና ሙስና ተስተውሎባቸዋል ሲሉ ምእመናን ክስ የመሰረቱባቸው የባህርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አመራሮች በህዝቡ እንዲነሱ ተደርጓል።

ምእመኑ በአስተዳዳሪው ላይ ከፍትህ አካላት እስከ ሃገሪቱ ሊቀ ጳጳሳት ድረስ አቤቱታ ቢያሰሙም መፍትሄ በማጣታቸው የራሳቸውን እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸው ታውቋል።

የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዩርጊስ ገዳም ዋና አሰዳዳሪ ቆሞስ አባ ወልደ ሃና ፀጋው ላለፊት  ሶስት ዓመታት ከመሩት ገዳም ከ32 በላይ የክስ መረጃዎች ቀርቦባቸው ተሰናብተዋል።

ምእመኑ ካቀረባቸው ክሶች መካከል  በሰንበት ትምህርት ቤት የተዳራጁ ወጣቶችን መበትን ፤የምእመኑን ማህበር ከስራ ውጭ ማድረግ ፤የቤተከርስቲያኑ የገቢ ወጭ ስራዎችን በግል ማከናወን ፤ የቅንጦት እቃዎችን በአንዴ እስከ 35000 ብር ወጭ በማድረግ ለግል ጥቅም ማዋል እና የልማት ስራዎች እንዳይሰሩ ማደናቀፍ የሚሉት ይገኙበታል።

በራስ አገዝ የሚንቀሳቀሱ ገዳመት ላይ በወር እስከ 75 ሺ ብር የሚደርስ ኪሳራ እንዲደርስ ምክንያት መሆናቸውም ተገልጿል።