ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አካሄዱ

የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መብታቸው እንዲከበርላቸው ለአመታት ሲጠይቁ የቆዩት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከአርብ ቀን ጸሎት በሁዋላ የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎችን በመልቀቅ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።ፍልውሃ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ በተካሄደው ተቃውሞ “ጭቆናን እንታገላለን፣ ኮሚቴው ይፈታ ፣ ድራማው ይብቃ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ተለቀዋል።