ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ወገኖች ጋር ተባብሮ ትግሉን እንዲያካሂድ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን የፍርድ ውሳኔ አውግዟል።
“ስርዓቱ ለመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው እውቅና ሰጥቶ ሲደራደር” ከቆየ በሁዋላ ፣ አሸባሪ ብሎ መክሰሱ፣ ‹‹ሽብር›› የሚባለው ክስ ስርዓቱ ያልፈለገውን የሚያስርበት ፍርድ ቤቱና ህጉም የአገዛዙ ዋነኛ መሳሪያ ሆነው መቀጠላቸውን ያመላክታል ብሎአል።
በኮሚቴው ላይ የተወሰደው እርምጃ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ይበልጡን ትግሉን አጠናክሮ፣ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ተባብሮ አምባገነንነትን ከምንጩ ከማድረቅ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑንም ሰማያዊ በመግለጫው ጠቅሷል። የሙስሊሙ ማህበረሰብ የፖለቲካ ትግሉን እንዲቀላቀል ፓርቲ ጥሪውን አቅርቧል።