መድረክ ታህሳስ 5 የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች እያደናቀፉት ነው

ታኀሳስ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ለመጠየቅ መድረክ የፊታችን እሁድ የጠራው ሰልፍ እንዲደናቀፍ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተጽእኖ ቢያሳርፉም፣ ተጽኖውን ሁሉ ተቋቁሞ የሰፈር ለሰፈር ቅስቀሳውን እያካሄደ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጥላሁን እንዳሻው ተናግረዋል።

አዲስ አበባ መስተዳድር ሰላማዊ ሰልፉ እንዲካሄድ እውቅና ቢሰጥም፣ ቅስቀሳ ለማድረግ ሌላ እውቅና ያስፈልጋል በሚል በድምጽ ማጉያ ቅስቀሳ ለማድረግ አለመቻሉን እንዲሁም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ አባሎቻቸው በተደጋጋሚ ለተወሰኑ ሰአታት እየታሰሩ እንደተለቀቁ አክለዋል

መድረክ እሁድ የሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ በወረዳ 8 ከጧቱ 3 ሰአት እስከ ቀኑ 7 ሰአት ይካሄዳል።