ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ ክርክር በታየበት የመድረክ ጉባኤ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት ማንፌስቶውንና መተዳደሪያ ደንቡን አጽድቀዋል። ባለ 25 ገጹ ማንፌስቶ ላለፉት ስድስት ወራት ሲዘጋጅ የቆየ ሲሆን ከ6 ሰአት በላይ በፈጀ ክርክር ጸድቋል:፡፡ ላለፉት 4 አመታት ሲንከባለል የቆየውና የድርጅቶች የልዩነት ምንጭ ተደርጎ ይታይ የነበረው መተዳደሪያ ደንብም እንዲሁ ጸድቋል።
“በጣም ደስ የሚል ኢትዮጵያዊ መድረክ ነበር፣ ቋንቋው፣ ቀለሙ፣ አመለካከቱ፣ ሁሉም አንድ ቋንቋ ሲናገር ለመጀመሪያ ጊዜ ተመለከትን” በማለት አንድ ተሳታፊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
መድረክ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ የፈጠሩት ግንባር ነው።
ድርጅቱ አቶ ጥላሁን እንዳሻው በሊቀመንበርነት እንዲቆዩ ወስኗል።