መከላከያ የባንክ ባለቤት ሊሆን ነው

፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጲያ መግስት ለ2005 የበጀት ጥቅምት

አመት ከያዛችው ዋንኛ የሰራ እቅዶች መካከል ወታደራዊ ባንክ ማቋቋም መሆኑን አስታውቆል።ሪፖርተር ከአዲስ አበባ እንደዘገበው መከላኪያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ባንኩን ለማቋቋም እየሰራ ነው። በተያዘውም አመት ተጠናቆ ሰራ ይጀምራል ብሏል።የመከላኪያ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ባቀረበው የስራ ክንውንና ዕቅድ ሪፖርት ላይ ይፋ የሆነው ወታደራዊ ባንክ ግንባታ በዋነኝነት ወታደራዊ  ቁልፍ ስልጣኖችን በእጁ ያደረገው ህውሃት ሃገሪቱን ወታደራዊ በሆኑ ተቋም ለመዝረፍ ሌላ ዘዴ መቀየሱን አንድ አንድ ወገኖች ከወዲሁ እየገለፀ ነው።ይሁን እንጂ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ለምክር ቤቱ እንደተናገሩት ባንኩ በዋነኝነት የሰራዊቱን አባላት የግል ቤት  ባለቤት ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።ይህ ሽፋን ነው የሚሉት የውጭ ታዛቢ ኢትዮጲያኖች የቤት ባለቤት የሚያደርጓቸውም ቢሆን የህዋቶቹን ከፍተኛ ወራደራዊ መኮንኖችና በተዋረድ ላሉ የእነሱ ሰዎች ብቻ ነው ባዮች ናቸው።

ከወዲሁ አወዛጋቢ የሆነው የመከላኪያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ባንክ ምስረታ ህጋዊነት ለብሄራዊ ባንክ የቀረበ የስራ ፍቃድ አለመኖሩንም የብሄራዊ ባንክን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አለማየሁ ከበደን ዋቢ ያደረግው ሪፖርተር ዘግቧል።ወታደራዊ ተቋም የባንክ ባለቤት እንዲሆን የብሄራዊ ባንክ ህግ መፍቀድ አለመፍቀዱ ያልተብራራ ቢሆንም አንድ ባንክ ሲመሰረት ከብሄራዊ ባንክ ጋር መመካከር እና ማሟላት የሚገባውን የስራ ፍቃድ ጨምሮ ማሟላት ያለበት ቢሆነም መከላኪያ ሚኒስቴር ይህንን ደንብ ያለመከተሉ የተለመደ የማን አለብኝነት አሰራር ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተችተዋል።