መንግስት የግል ትምህርት ቤቶችን መውረሱን አመነ::

ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በአዲስ አበባ የሚገኙ ከ102 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች መወረሳቸውን መንግስት አምኖአል።

ኢሳት ከወራት በፊት፣ ራሳቸውን ማስተዳዳር የሚችሉ ትምህርት ቤቶች ወደ መንግስት እንደዞሩ ዘገባ በሰራበት ወቅት፣ መንግስት ዜናውን ሲያስተባብል ነበር።

ይሁን እንጅ የአዲስ አበባ መስተዳዳር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከ102 በላይ ትምህርት ቤቶች ወደ መንግስት መዞራቸውን ገልጧል።

መንግስት በትምህርት ቤቶች ውስጥ የዘረጋውን የአንድ ላምስት የቁጥጥር ሰንሰለት በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ መዘርጋት ባለመቻሉ ትምህርት ቤቶችን ለመውረስ እንደተገደደ መዘገባችን ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide