የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማህበራዊ ድረገጾች የተለቀቀው ይህ መረጃ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ አበባ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበ ነው። ወንጀል ዝርዝር በሚለው ክፍል ውስጥ ” 2ኛ ተከሳሽ መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም፣ ሳይፈቀድለት የነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊ ሙስሊም እንዳይሰገድ በማድረግና መስኪዱ በመታወቁ በወና ወንጀል አድራጊነት ተከሷል” ይላል
ምንም እንኳ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ እንደማይገባ ህገመንግስቱን በመጥቀስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቢቆይም፣ ሰነዱ መንግስት የሃይማኖት መሪዎችን እስከመሾም የሚደርስ እርምጃ መውሰዱን ሰነዱ ያመለክታል።